ከእነርሱም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ በተራሮችም ላይ የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ የሕዝቡንም ሥራ ለሚቆጣጠር የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።
ነህምያ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያን ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ጎልማሶች ሥራ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጋሻ፥ ጦር፥ ቀስትና ጥሩር ይይዙ ነበር፤ ሹማምቱም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ፣ “የሠራተኞቹ ጕልበት እየደከመ ነው፤ ከፍርስራሹም ብዛት የተነሣ ቅጥሩን መልሰን ለመሥራት አንችልም” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች “የሸክም ሥራ እያደከመን ሄደ፤ ገና መነሣት ያለበት ፍርስራሽ ብዙ ነው፤ ቅጽሩን እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም፥ “የተሸካሚዎች ኀይል ደከመ፤ ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም፦ የተሸካሚዎች ኃይል ደከመ፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፥ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም አሉ። |
ከእነርሱም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ በተራሮችም ላይ የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ የሕዝቡንም ሥራ ለሚቆጣጠር የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።
እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።
የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ ሠራዊቱን ጽኑ ሥራ አሠራ፤ ራስ ሁሉ ተመልጧል፥ ትከሻም ሁሉ ተልጦአል፥ ሆኖም በእርሷ ላይ ለሰሩት ሥራ እርሱም ሆነ ሠራዊቱ ከጢሮስ ደመወዝ አልተቀበሉም።