ነህምያ 11:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሺሎናዊው ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የሐዛያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ ማዓሤያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሴሎ ዘር የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የፆዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኮልሖዜ የልጅ ልጅ የሆነው የባሩክ ልጅ ማዕሤያ ሌሎች የቀድሞ አባቶቹ የይሁዳ ልጅ የነበረው የሼላ ዘሮች የሆኑትን ሐዛያን፥ ዓዳያን፥ የዮያሪብንና ዘካርያስን ይጨምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴሎ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ መዕሤያ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። |
ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤
የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።