ነህምያ 11:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ልጅ ከዜራሕ ወገኖች የምሼዛቤል ልጅ፥ ፕታሕያ ሕዝቡን በሚመለከት ጉዳይ ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ልጅ የዛራ ዘር የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ሕዝቡን በሚመለከት ጕዳይ ሁሉ የንጉሡ ተወካይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ነገድ የዛራ ጐሣ ተወላጅ የሆነው የመሼዛቤል ልጅ ፐታሕያ የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት ጉዳይ የፋርስ ንጉሥ እንደ ራሴ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የባስያዘብኤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ። |
“ሥራቸውም የጌታን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ በሚሰጡተት አገልግሎት አሮንን ልጆች መርዳት፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት መሥራት ነበረ።
በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።