ነህምያ 10:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰብላችንንና የእያንዳንዱን ዛፍ ፍሬ በኵራትም ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማምጣት ቃል እንገባለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእህላችንን መከር በምንሰበስብበት ወቅትና የዛፎቻችንን ፍሬ በምንለቅምበት ወራት በመጀመሪያ የደረሰውን እሸት፥ ወደ ቤተ መቅደስ እያመጣን እናበረክታለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየዓመቱም የመሬታችንን በኩራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኩራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥ |
የበኩራቱ ሁሉ መጀመሪያ፥ ስጦታ ሁሉ፥ ስጦታዎቻችሁ ሁሉ፥ ለካህናት ይሆናል፤ በቤትህም ውስጥ በረከት እንዲያድር የሊጣችሁን በኵራት ለካህን ትሰጣላችሁ።
ወይም በሐሰት የማለበትን ምንም ዓይነት ነገር ይመልስ፤ እርሱም የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን በሙሉ የወሰደውን ነገር ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ጨምሮበት ለባለቤቱ ይስጠው።
እንዲሁም አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ሳላችሁ ከአንተ ጋር በአንድነት እንዲሆኑ፥ እንዲያገለግሉህም፥ የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ደግሞ ከአንተ ጋር አምጣቸው።
ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።