Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 10:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የእህላችንን መከር በምንሰበስብበት ወቅትና የዛፎቻችንን ፍሬ በምንለቅምበት ወራት በመጀመሪያ የደረሰውን እሸት፥ ወደ ቤተ መቅደስ እያመጣን እናበረክታለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “የሰብላችንንና የእያንዳንዱን ዛፍ ፍሬ በኵራትም ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማምጣት ቃል እንገባለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በየ​ዓ​መ​ቱም የመ​ሬ​ታ​ች​ንን እህል ቀዳ​ም​ያት፥ የሁሉ ዓይ​ነት ዛፍ የፍሬ ቀዳ​ም​ያት ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እና​መጣ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በየዓመቱም የመሬታችንን በኩራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኩራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 10:35
13 Referencias Cruzadas  

መሥዋዕት የሚቃጠልበትን ማገዶ በተወሰነው ክፍለ ጊዜ ሁሉ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ አደራጀሁ፤ ሰዎቹም ከሚሰበስቡት ሰብል ሁሉ ከእህሉም ሆነ ከፍራፍሬው በመጀመሪያ የደረሰውን እንዴት ማቅረብ እንደሚገባቸው አዘጋጀሁ። አምላኬ ሆይ! ይህን ሁሉ አስብ፤ ይህን በማድረጌም ቸርነት አድርግልኝ።


“በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


“በየዓመቱ የመከራችሁን በኲራት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግም ሆነ የፍየል ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።”


የመከር መጀመሪያ የሆነውን ያማረውን በኲራትና ለእኔ የቀረበውን ስጦታ ሁሉ ካህናቱ ይውሰዱ፤ ሕዝቡም ሁልጊዜ እህል ሲፈጩ የዱቄቱን በኲራት ለካህናቱ መባ አድርገው ያበርክቱ፤ እኔም ይህንን ሁሉ የሚያደርጉትን ሕዝብ ቤታቸውን በበረከት እሞላዋለሁ።


ወይም በሐሰት ምሎ የወሰደውን ሁሉ አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለባለቤቱ ይክፈል።


ለበደሉም ማስተስረያ ምንም ነውር የሌለበት አንድ ተባዕት በግ ወይም በታወቀው ተመን የተተመነውን ገንዘብ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ።


“እስራኤላውያን የሚሰጡኝን ምርጥ የሆነ በኲራት፥ ይኸውም የወይራ ዘይት፥ የወይን ጠጅና እህል ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤


ከሚሰጥህ ምድር ከምታመርተው ምርት በኲራቱን በቅርጫት በማድረግ እግዚአብሔር አምላክህ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ቦታ ውሰድ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos