ናሆም 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በመካከልሽ ያለው ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፤ የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ በሰፊው ተከፍተዋል፥ መወርወሪያዎችሽን እሳት በልቶአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ ሁሉም ሴቶች ናቸው! የምድርሽ በሮች፣ ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቷቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችሽ ሁሉ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል፤ የጠረፍሽ በሮች ለጠላቶችሽ ክፍት ሆነዋል፤ መወርወሪያዎቹም እሳት በልቶአቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል። |
ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።
የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።