ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ ጌታን፥ “እነሆ፥ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ! የተሳሳትሁም እኔ ነኝ! እነዚህ በጎች ግን ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ” አለ።
ሚክያስ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን ስለ በደልሁ፣ እስኪቆምልኝ እስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቍጣ እቀበላለሁ፤ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ እኔም ጽድቁን አያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በድዬዋለሁ፤ ስለዚህም እርሱ የቀረበብኝን ክስ ተመልክቶ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቊጣውን እታገሣለሁ፤ በመጨረሻም እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ ፍትሕንም ይሰጠኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ። |
ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ ጌታን፥ “እነሆ፥ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ! የተሳሳትሁም እኔ ነኝ! እነዚህ በጎች ግን ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ” አለ።
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመጽ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።
እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።
ዳዊትም ናባል መሞቱን በሰማ ጊዜ፥ “የናባልን ስድብ የተበቀለልኝና እኔን አገልጋዩን ክፉ ከማድረግ የጠበቀኝ ጌታ ይመስገን፤ ናባል የሠራውንም ክፉ ነገር በራሱ ላይ መለሰበት” አለ። ዳዊትም አቢጌል ሚስት ትሆነው ዘንድ በመጠየቅ መልእክት ላከባት።