ሚክያስ 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትንሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንቺ የወታደር ከተማ ሠራዊትሽን አሰልፊ! ከበባው በእኛ ላይ ተጠናክሮአል፤ የእስራኤልንም መሪ ጒንጩ ላይ በበትር ይመቱታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ። |
ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የጌታ መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት።
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
እናንተ አሕዛብ፤ ፎክሩ፤ ግን ደንግጡ። በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤
ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፤ ድንቅ መካር፤ ኀያል አምላክ፤ የዘለዓለም አባት፤ የሰላም ልዑል ይባላል።
እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።