እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።
ሚልክያስ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ካህናት ሆይ፤ ስሜን የምታቃልሉት እናንተ ናችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል። |
እነሆ፥ የአገልጋዮች ዐይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የአገልጋዪቱም ዐይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ ጌታ አምላካችን ነው።
ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፤ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቁርባን አላስቸገርሁህም፤ በዕጣንም አላደከምሁህም።
በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።
ካህናቶችዋም ሕጌን ጥሰዋል፥ ቅዱሳት ነገሮቼንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነ ነገርና በረከሰ ነገር ላይ ልዩነትን አላደረጉም፥ በርኩስ ነገርና በንጹሕ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም፥ ከሰንበቶቼ ዓይናቸውን ሰወሩ፥ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
የሁላችን አባት አንድ አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማርከስ ሁላችንም ለምን ወንድማችንን እናታልላለን?
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ በምድረ በዳም፥ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ፥ ጌታ አምላካችሁ እንዴት እንደተንከባከባችሁ አይታችኋል።’
አንተ የማታስተውልና ኀሊና ቢስ ሕዝብ፥ ለጌታ ምላሽህ እንዲህ ነው? እርሱ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና የሠራህ ያጸናህም እርሱ አይደለምን?”
“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።