ሉቃስ 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ተሸክሞ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በትከሻው ይሸከመውና መልሶ ያመጣዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በትከሻው ላይ ይሸከማታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ |
በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።
የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።