ሉቃስ 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ፤’ ይላቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹንም በአንድነት ጠርቶ፣ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችሁ’ ይላቸዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ወደ ቤቱም በደረሰ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼአለሁና ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ!’ ይላቸዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን ጠርቶ፦ የጠፋችኝን በጌን አግኝቼአታለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦ የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። Ver Capítulo |