ዘሌዋውያን 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ወይፈን አመጣ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሙሴ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበውን ኰርማ አመጣ፤ አሮንና ልጆቹ በኰርማው ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኀጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። |
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከደሙ ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹ፥ በእርከኑ፥ በአራቱ ማዕዘን ላይ፥ በዙሪያውም ባለው ጠርዝ ላይ ታደርጋለህ፤ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታጠራዋለህም።
አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ያደርገዋል።
“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤
ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ማስተስረያ እንዲሆኑ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ አቅርብ።
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።