ሕዝቅኤል 43:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በፊቴ ቀርበው ለሚያገለግሉኝ ካህናት፣ ለሌዋውያኑ ለሳዶቅ ቤተ ሰብ የኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ወይፈን ስጥ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በፊቴ ቆመው እኔን ለሚያገልገሉ የሌዊ ነገድ ከሆነው ከሳዶቅ ዘር ለተወለዱ የኃጢአት ሥርየት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ዘንድ ለእነርሱ አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፤’ ይላል ልዑል እግዚአብሔር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ከመንጋው አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítulo |