ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
ዘሌዋውያን 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበሬው ወይም የበጉ የአካሉ ክፍል ረጅም ወይም አጭር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካሉ የጐደለ ወይም ቅርጹ የተበላሸ እንስሳ የበጎ ፈቃድ መሥዋዕት ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፤ ነገር ግን ስእለት የተፈጸመለት ሰው መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተቈረጠ ቢሆን፥ ቈጥረህ የራስህ ገንዘብ አድርገው እንጂ ለስእለት አይቀበልህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬው ወይም በጉ የተጨመረበት ወይም የጐደለበት ነገር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም። |
ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
ዓይነ ስውር ወይም የተሰበረ ወይም አካለ ጎዶሎ ወይም የሚመግል ቁስል ወይም የእከክ ደዌ ያለበት ወይም ቋቁቻ የወጣበት ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለጌታ አታቅርቡ፤ እነርሱንም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ በመሠዊያው ላይ ለጌታ አትሠዉ።
“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።
አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤