Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አካሉ የጐደለ ወይም ቅርጹ የተበላሸ እንስሳ የበጎ ፈቃድ መሥዋዕት ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፤ ነገር ግን ስእለት የተፈጸመለት ሰው መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የበሬው ወይም የበጉ የአካሉ ክፍል ረጅም ወይም አጭር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በሬው ወይም በጉ የተጨመረበት ወይም የጐደለበት ነገር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 22:23
7 Referencias Cruzadas  

ወንዶችና ሴቶች የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ላዘዘው ሥራ የሚውል ልባቸው የፈቀደውን ስጦታ ለእግዚአብሔር አመጡ።


የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው፥ ይኸውም ዕውር ወይም አንካሳ የሆነ፥ መልኩ ወይም ቅርጹ የተበላሸ፥


ዕውር፥ ሰባራ ወይም ጉንድሽ የሆነ ወይም የሚመግል ቊስል፥ እከክ ወይም ሽፍታ ያለበት ማናቸውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።


ብልቱ የተበላሸ እንስሳ ለእግዚአብሔር በምድርህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።


ለመሆኑ የታወረውን፥ የታመመውንና አንካሳ የሆነውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ በደል የፈጸማችሁ አይመስላችሁምን? ይህን የመሰለ እንስሳ ለአለቃችሁ ገጸ በረከት አድርጋችሁ ብታቀርቡለት፥ ደስ ብሎት የሚቀበላችሁና የሚያመሰግናችሁ ይመስላችኋልን?” ይላል የሠራዊት አምላክ።


ነገር ግን እንስሶቹ እንከን ቢገኝባቸው ይኸውም ሽባ ወይም ዕውር ቢሆኑ፥ ወይም ደግሞ የባሰ ነውር ቢኖርባቸው፥ እነርሱን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።


“ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች መካከል አንዳች ነውር ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos