ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
ዘሌዋውያን 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በሕዝቡ መካከል ዘሩን አያርክስ፤ እኔ የምቀድሰው ጌታ ነኝና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ካልሆነ ግን በሕዝቡ መካከል ልጆቹ የረከሱ ይሆናሉ፤ የምቀድሰው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም የምቀድሰው እግዚአብሔር ነኝና በሕዝቡ መካከል ዘሩን አያጐስቍል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም የምቀድሰው እግዚአብሔር ነኝና በሕዝቡ መካከል ዘሩን አያጐስቍል። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
አንዳንድ ሴቶች ልጆቻቸውን ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስት አድርገው ወስደዋል፥ ቅዱሱንም ዘር ከምድር ሕዝቦች ጋር ደባልቀዋል፤ በዚህ አለመታመን የአለቆቹና የባለሥልጣኖቹ እጅ ቀዳሚ ነበር።”
ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንድ ልጆችህ ብትወስድ፥ ሴቶች ልጆቻቸው አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ልጆችህን ከአምላኮቻቸው ጋር እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።
ባልዋ የሞተባትን፥ ወይም የተፈታችውን፥ ወይም የረከሰችውን፥ ወይም አመንዝራይቱን አያግባ፤ ነገር ግን ከሕዝቡም መካከል ከወገኑ ድንግሊቱን ያግባ።
ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኩሰት ሠርቷል፤ ይሁዳ ጌታ የወደደውን መቅደስ አርክሶአል፥ የባዕድንም አምላክ ልጅ አግብቶአል።
አንድ አላደረጋቸውምን? የመንፈስም ቅሪት ለእርሱ ነው? አንዱስ ምን ፈልጎ ነው? የእግዚአብሔርን ዘር ፈልጎ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።
ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፤ ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች፤ እንደዚህ ካልሆነ ግን፥ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ እንደዚህ ከሆነ ግን የተቀደሱ ናቸው።