Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በኩራቱም ቅዱስ ከሆነ ብኮው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በኵር ሆኖ የቀረበው የቡሖው ክፍል ቅዱስ ከሆነ፣ ቡሖው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩ ቅዱስ ከሆነ፣ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከአንድ ዐይነት ሊጥ የመጀመሪያው ክፍል የተቀደሰ ከሆነ ሊጡ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ እንዲሁም የአንድ ዛፍ ሥሩ የተቀደሰ ከሆነ ቅርንጫፎቹም የተቀደሱ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በኵራቱም ቅዱስ ከሆነ ብሆው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 11:16
17 Referencias Cruzadas  

ለፍጥረቱ የበኵራት እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


የበኩራቱ ሁሉ መጀመሪያ፥ ስጦታ ሁሉ፥ ስጦታዎቻችሁ ሁሉ፥ ለካህናት ይሆናል፤ በቤትህም ውስጥ በረከት እንዲያድር የሊጣችሁን በኵራት ለካህን ትሰጣላችሁ።


ከሀብትህ አስበልጠህ ጌታን አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት ይልቅ፥


እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?


ነገር ግን ከቅርንጫፎቹ አንዳንዱ ቢሰበሩ አንተም የበረሃ ወይራ የሆንህ በመካከላቸው ገብተህ ከእነርሱ ጋር የወይራ ዘይት ከሚወጣው ሥር ተካፋይ ከሆንህ፥


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከሩን ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤


እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ።


የእህልህን፥ የአዲሱን ወይንህንና የዘይትህን በኵራት እንዲሁም ከበጎችህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣለህ፤


የመከር በዓል፥ በእርሻህ የዘራኸውን የፍሬህን በኵራት፥ ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ በምትሰበስብበት ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።


እነዚህ ከሴቶች ጋር ያልረከሱ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበትም የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፤ ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች፤ እንደዚህ ካልሆነ ግን፥ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ እንደዚህ ከሆነ ግን የተቀደሱ ናቸው።


የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ከበሬህና ከበግህም እንዲሁ አድግር፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፥ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።


ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios