La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 20:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማናቸውም ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ የወር አበባዋን ኀፍረት ገልጠዋል ሁለቱም ከሕዝቡ ተለይተው ይባረሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማና​ቸ​ውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ፈሳ​ሽ​ዋን ገል​ጦ​አ​ልና፥ እር​ስ​ዋም የደ​ም​ዋን ፈሳሽ ገል​ጣ​ለ​ችና ሁለቱ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ተለ​ይ​ተው ይጥፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማናቸውም ሰው ከባለ መርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርስዋም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 20:18
6 Referencias Cruzadas  

እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’”


በተራሮች ላይ ባይበላ፥ ዐይኖቹን ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ፥ የባልንጀራውን ሚስት ባያረክስ፥ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፥


በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ዕራቁትነት ገለጡ፥ በአንቺም ውስጥ አደፍ ያለባትን አዋረዱ።


ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ እንደ ወር አበባዋም ጊዜያት ትረክሳለች።


ማንም ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ የወር አበባዋ ቢነካው፥ እርሱ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።


“እርሷም ርኩስ በሆነችበት የወር አበባዋ ጊዜያት ላይ ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ ወደ ሴት አትቅረብ።