Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 30:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ተመሳሳይ ዐይነት የሠራና ከካህናት ሌላ በማንም ሰው ላይ ያፈሰሰ ሁሉ ከወገኑ ይወገድ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራ ወይም ከዚህ ቅባት ወስዶ ካህን ያልሆነውን ሰው የሚቀባ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።’ ”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እንደ እርሱ ያለ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፥ በሌ​ላም ሰው ላይ የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እንደ እርሱ ያለውን የሚያደርግ ሰው፥ በሌላም ሰው ላይ የሚያፈስሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:33
27 Referencias Cruzadas  

ለሽቶነት ፈልጎ እንደ እርሱ የሚሠራ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”


የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፥ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።”


ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።


ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ የፋሲካን በዓል ባያከብር፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ አላቀረበምና ያ ሰው ኃጢአቱን ይሸከማል።


በዚያም ቀን ራሱን የማያዋርድ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።


እርሱንም የሚበላ ማናቸውም ሰው ለጌታ የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና በደሉን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጠፋል።


ለጌታ ሊሠዋው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።


በጌታ ማደሪያ ፊት ለፊት ለጌታ እንደ ቁርባን አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።


በእነሱ እጃቸው ሙሉ እንዲሆንና የተቀደሱ እንዲሆኑ ማስተስረያ የሆነውን ነገር ይብሉት፤ የተቀደሰ ስለሆነ ሌላ ሰው አይብላው።


ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገሩ ተወላጅ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይወገድ።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መልካም መዓዛ ያለው ቅመም፥ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ንጹሕ እጣን ለራስህ ውሰድ፥ ሁሉም እኩል መጠን ይኑራቸው፤


ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰው ፈጽሞ ይገደል፥ በእርሷ ሥራን የሚሠራ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።


“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


“ሥጋን የለበሰ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ሕይወቱ ደሙ ነውና ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አልሁ፦ ሥጋን የለበሰ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ሕይወቱ ደሙ ነውና የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ፤ የሚበላውም ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ።


በእርግጥ ማንም ሰው ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ነገሮች ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፥ ያደረጋችው ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።


መቅደሴን ለማርከስ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ለማንቋሸሽ ልጁን ለሞሌክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


“ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፤ ከሕዝባቸውም ልጆች ፊት ተለይተው ይጥፉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና በደሉን ይሸከማል።


ማናቸውም ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።


እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዳችሁ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ ሁሉ ርኩሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለጌታ ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱሳን ነገሮች ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


“የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤


ነገር ግን የአገሩ ተወላጅ ቢሆን ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በትዕቢት ማናቸውንም ነገሮች የሚያደርግ ሰው ጌታን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።


የጌታን ቃል ስለ ናቀ፥ ትእዛዙንም ስላፈረሰ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ በደሉ በራሱ ላይ ነው።”


የሞተውን ሰው በድን የነካ ማናቸውም ሰው ሁለመናውን ባያነጻ የጌታን ማደሪያ ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ ከርኩሰት የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኩሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።


“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios