ዘሌዋውያን 17:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ እንዲሆን እኔ ለእናንተ ሰጠሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማንኛውም ሕያው ፍጥረት ሕይወት የሚገኘው በደሙ ውስጥ ነው፤ ደሙ በመሠዊያው ላይ ለእናንተ ኃጢአት ማስተስረያ እንዲሆን ሰጥቻችኋለሁ፤ ደምም ሕይወት ስለ ሆነ የኃጢአት ማስተስረያ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት። |
በሬውንም በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
“አሮንም ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፤ ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያርዳል።
“ሥጋን የለበሰ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ሕይወቱ ደሙ ነውና ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አልሁ፦ ሥጋን የለበሰ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ሕይወቱ ደሙ ነውና የሥጋውን ሁሉ ደም አትብሉ፤ የሚበላውም ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ።
ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ እንዲያስተሰርይለትም ቀደሰው።
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥