ሮሜ 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተሰረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ፥ በደሙም የሆነ ማስተስረያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም ከጥንት ጀምሮ በበደሉት ላይ ጽድቁን ይገልጥ ዘንድ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ Ver Capítulo |