ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ዘሌዋውያን 11:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ጌታ ነኝ፤ ስለዚህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስለዚህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስለዚህም እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታሳድፉ። እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ። |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ።
ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።”
ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና ጌታን ማገልገል አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።