ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 11:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም የሞተው በማናቸውም ነገር ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቆዳ ወይም ከረጢት ቢሆን ለማናቸውም ሥራ የሚጠቅም ዕቃ ሁሉ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ግን ይነጻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድኑ በማንኛውም ዕቃ ላይ ቢወድቅ ያ ዕቃ ከዕንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቈዳ ወይም ከበርኖስ የተሠራ ከረጢት ቢሆን ርኩስ ይሆናል፤ በውሃ ውስጥ ይደረግ፤ ሆኖም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድናቸው የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ይኸውም ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ልብስን፥ ቆዳን ወይም ከረጢት የመሳሰሉትንና ሌላውንም ነገር ሁሉ ይጨምራል፤ የእነርሱ በድን የነካው ይህን የመሰለ ዕቃ ሁሉ በውሃ ውስጥ ተነክሮ ይቈይ፤ እስከ ምሽትም ድረስ ርኩስ ሆኖ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በድናቸው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱን በውኃ ውስጥ ይንከሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም የሞተው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቁርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። |
ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።
የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።