ሰቈቃወ 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሯል፤ በራብም ተቃጥሏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከራብ ጽናት የተነሣ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራብ የተነሣ ሰውነታችን ጠወለገ፤ ቍርበታችንም እንደ ምድጃ ጠቈረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። |
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።