መሳፍንት 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጉልበታቸው ተንበረከኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጕልበታቸው ተንበረከኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ የሚጠጡት ቊጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀሩት ሁሉ የጠጡት ግን በጒልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጃቸውም ውኃ ወደ አፋቸው አድርገው የጠጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕልበታቸው ተንበረከኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጃቸውም ውኃ ወደ አፋቸው አድርገው የጠጡት ቁጥር ሦስት መቶ ነበረ፥ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ። |
ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዞአቸው ወረደ፤ እዚያም ጌታ፥ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፥ በምላሳቸው የሚጠጡትን፥ በጉልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው።
ጌታም ጌዴዎንን፥ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችሃለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው።