መሳፍንት 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ጌታም ጌዴዎንን፥ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችሃለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፣ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደ የመጡበት ይመለሱ” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እግዚአብሔር ጌዴዎንን “በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አማካይነት አድናችኋለሁ፤ በምድያማውያን ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ፤ ለቀሩት ግን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ንገራቸው” አለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያምንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፥ ምድያማውያንንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፥ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ አለው። Ver Capítulo |