መሳፍንት 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዞአቸው ወረደ፤ እዚያም ጌታ፥ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፥ በምላሳቸው የሚጠጡትን፥ በጉልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዟቸው ወረደ፤ እዚያም እግዚአብሔር፣ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፣ በምላሳቸው የሚጠጡትን፣ በጕልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ጌዴዎንም ሰዎቹን ወደ ወንዝ ውሃ አወረዳቸው፤ እግዚአብሔርም “በጒልበቱ ተንበርክኮ ውሃ ከሚጠጣው መካከል እንደ ውሻ በምላሱ እየጨለፈ የሚጠጣውን ሁሉ ለየው!” አለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረደ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ በምላሱ የሚጠጣውን ሁሉ፥ እርሱን ለብቻው አድርገው፤ እንዲሁም ሊጠጣ በጕልበቱ የሚንበረከከውን ሁሉ ለብቻው አድርገው” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረደ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ በምላሱ የሚጠጣውን ሁሉ፥ እርሱን ለብቻው አድርገው፥ እንዲሁም ሊጠጣ በጉልበቱ የሚንበረከከውን ሁሉ ለብቻው አድርገው አለው። Ver Capítulo |