Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ የሚጠጡት ቊጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀሩት ሁሉ የጠጡት ግን በጒልበታቸው ተንበርክከው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጕልበታቸው ተንበረከኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጉልበታቸው ተንበረከኩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በእ​ጃ​ቸ​ውም ውኃ ወደ አፋ​ቸው አድ​ር​ገው የጠ​ጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕ​ል​በ​ታ​ቸው ተን​በ​ረ​ከኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በእጃቸውም ውኃ ወደ አፋቸው አድርገው የጠጡት ቁጥር ሦስት መቶ ነበረ፥ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:6
4 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ ከመንገድ ዳር ካለው ምንጭ ከጠጣ በኋላ፥ ኀይሉን በማደስ በድል አድራጊነት ጸንቶ ይቆማል።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል።


ጌዴዎንም ሰዎቹን ወደ ወንዝ ውሃ አወረዳቸው፤ እግዚአብሔርም “በጒልበቱ ተንበርክኮ ውሃ ከሚጠጣው መካከል እንደ ውሻ በምላሱ እየጨለፈ የሚጠጣውን ሁሉ ለየው!” አለው።


እግዚአብሔር ጌዴዎንን “በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አማካይነት አድናችኋለሁ፤ በምድያማውያን ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ፤ ለቀሩት ግን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ንገራቸው” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos