በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።
መሳፍንት 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስት ቡድን የተከፈሉት ሰዎች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ማሰሮቻቸውንም ሰበሩ፤ ችቦዎቻቸውን በግራ እጆቻቸው፥ ቀንደ መለከቶቻቸውንም በቀኝ እጆቻቸው ይዘው፥ “የጌታና የጌዴዎን ሰይፍ” በማለት ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስት ቡድን የተከፈሉት ሰዎች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ማሰሮዎቻቸውንም ሰበሩ፤ ችቦዎቻቸውን በግራ እጆቻቸው፣ የሚነፏቸውንም ቀንደ መለከቶች በቀኝ እጆቻቸው ይዘው፣ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” በማለት ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌላም በኩል የነበሩት ሁለቱ ክፍሎች እንዲሁ አደረጉ፤ ሁሉም የተለኰሱትን ችቦዎቻቸውን በግራ እጃቸው፥ እምቢልታቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን እንዋጋለን!” እያሉ በመጮኽ ደነፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ ማሰሮዎችንም ሰበሩ፤ በግራ እጃቸውም ችቦዎችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ፥ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፥ ማሰሮችንም ሰበሩ፥ በግራ እጃቸውም ችቦችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ፦ የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ ብለው ጮኹ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።
አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።
ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ በቀጥታ አቅንቶ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ያዝዋት።
ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ።
በማግስቱ ሳኦል ሠራዊቱን ከሦስት ቦታ ከፈለው፤ ሊነጋጋ ሲል የአሞናውያንን ሰፈር ጥሰው በመግባት ፀሓይ ሞቅ እስኪል ድረስ ፈጇቸው። በሕይወት የተረፉትም ሁለት እንኳን ሆነው በአንድ ላይ ሊሆኑ እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።