Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሰባት ካህናት፣ ሰባት ቀንደ መለከት ተሸክመው በታቦቱ ፊት ይውጡ፤ በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ መለከት እየነፉ ከተማዪቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እያንዳንዳቸው እምቢልታ የያዙ ሰባት ካህናት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ በሰባተኛው ቀን ካህናቱ እምቢልታ እየነፉ አንተና ወታደሮችህ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ትዞሩአታላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፥ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 6:4
33 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።


አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው።


ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤


ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤


እነሆም፥ ጌታ በእኛ ላይ አለቃ ነው፥ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፥ በእናንተም ላይ የጦርነት ማስጠንቀቅያ ድምፅ ያሰማሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ! አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከጌታ ጋር አትዋጉ።”


እናንተ በዚህ ውግያ ላይ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ! ተሰለፉ፥ ጸንታችሁም ቁሙ፥ የሚሆነውንም የጌታን ድል አድራጊነት እዩ፤’ ጌታም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥ ነገም በእነርሱ ላይ ውጡ።”


ሌዋውያንም፥ የቀዓት ልጆችና የቆሬ ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን እጅግ ታላቅ በሆነ ድምፅ ሊያመሰግኑት ቆሙ።


ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፦ “ጽኑ ፍቅሩ ለዘዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ” የሚሉትንም ጌጠኛ ልብስም ለብሰው የሚያመሰግኑትን፥ ለጌታም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።


አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


ካህኑም በግራ እጁ መዳፍ ላይ ያለውን ዘይት በቀኝ ጣቱ ነክሮ ከዘይቱ በጌታ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል።


ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመቅደሱ መጋረጃ ትዩዩ ደሙን ሰባት ጊዜ ይረጫል።


እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።


እርሱም መልሶ፦ “ለዘሩባቤል የተባለው የጌታ ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በለዓምም ባላቅን፦ “ሰባት መሠዊያ በዚህ ሥራልኝ፥ ሰባትም ወይፈን ሰባትም አውራ በግ በዚህ አዘጋጅልኝ” አለው።


ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በጌታ ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፤ ተዋጊዎቹም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፤ የኋላ ደጀንም የሆነው ሕዝብ ከጌታ ታቦት በኋላ ይመጡ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።


እናንተም ከተማይቱን ትዞሩአታላችሁ፥ ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ ከተማይቱን በቀን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።


ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ እርሷ አቅንቶ በቀጥታ ይገባል።”


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”


ከዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች በየድምፃቸው ተናገሩ።


ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።


ከአራቱም ሕያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው እግዚአሔር ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።


ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።


በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።


በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።


ሰባቱንም መለከት የያዙ ሰባቱ መላእክት ሊነፉ ተዘጋጁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos