መሳፍንት 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ ጌታን አመስግኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎች እስራኤልን ስለ መሩ፥ ሕዝቡም በፈቃደኛነት ራሱን ስላቀረበ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ውስጥ መሳፍንት ስለ መሩ ሕዝቡም ስለ ፈቀዱ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ። |
“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”
በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፥ ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፥ የጌታንም ጽድቅ፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።”