Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 94:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የበቀል አምላክ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ የበቀል አምላክ ሆይ፤ ደምቀህ ተገለጥ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በቀልን የምትመልስ አምላክ ነህ፤ ስለዚህ ፍርድህን ግለጥ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ለን፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንና ለመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንም እልል እን​በል፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 94:1
14 Referencias Cruzadas  

ፈሪ ልብ ላላቸው፦ “እነሆ፥ አምላካችሁ ለበቀል፥ ብድራት ለመመለስ ይመጣል፤ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ!” በሉአቸው።


ጌታ ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ ጌታ ተበቃይና መዓት የተሞላ ነው፤ ጌታ ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፤ ቁጣን ለጠላቶቹ ያቆያል።


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።


ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፥ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቁር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፥ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።


በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል።


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤” ያለውን እናውቃለን፤ ደግሞም “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።”


የአምላካችንን የጌታን በቀል ስለ መቅደሱም ሲል የሚበቀለውን በቀል በጽዮን ለመናገር ከባቢሎን ምድር የሚመጡትን የኰብላዮችና የስደተኞች ድምፅ አድምጡ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።


ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ እግዚአብሔር ያበራል።


አንተም የአክዓብ ልጅ የሆነውን ጌታህን ንጉሡን መግደል አለብህ፤ በዚህም ዓይነት የእኔን ነቢያትና ሌሎችንም አገልጋዮቼን የገደለችውን ኤልዛቤልን እበቀላታለሁ፤


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios