አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”
መሳፍንት 16:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ። አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሶምሶን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አስበኝ፤ አምላኬ ሆይ! እባክህ ኀይል ስጠኝና ፍልስጥኤማውያን ዐይኖቼን ስላወጡ አንድ ጊዜ ብቻ እንድበቀላቸው አድርገኝ!” ብሎ ጸለየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስበኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበርታኝ፤ እንግዲህ ስለ ሁለቱ ዐይኖቼ ፋንታ ከፍልስጥኤማውያን አንዲት በቀልን እበቀላለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶምሶንም፦ ስለ ሁለቱ ዓይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አሁን እንድበቀል፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እባክህ፥ አስበኝ፥ አምላክ ሆይ፥ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ፥ እባክህ፥ አበርታኝ ብሎ እግዚአብሔርን ጠራ። |
አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።
ከዚህ በላይ ምን ልበል? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሳምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤልና ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።
እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ ጌታ ጮኸ።
በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።