Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 16:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺሕ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በሕንጻውም ውስጥ ብዙ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም የፍልስጥኤም ገዢዎች ሁሉ ነበሩ፤ በሰገነት ላይ ሆነው ሶምሶን ሲያጫውታቸው የሚመለከቱ ሦስት ሺህ ወንዶችና ሴቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በቤ​ትም ውስጥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሞል​ተ​ው​በት ነበር፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ፤ በቤ​ቱም ሰገ​ነት ላይ ሶም​ሶን ሲጫ​ወት የሚ​ያዩ ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በቤትም ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ሞልተውበት ነበር፥ የፍልስጥኤምም መኳንንት ሁሉ በዚያ ነበሩ፥ በቤቱም ሰገነት ላይ ሶምሶን ሲጫወት የሚያዩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:27
6 Referencias Cruzadas  

አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።


“አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት።


እነርሱም ከመተኛታቸው በፊት ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች።


ሳምሶን እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፥ “ቤተ ጣዖቱ ደግፈው ወደ ያዙት ምሰሶዎች አስጠጋኝና ልደገፋቸው” አለው።


ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”


ሆኖም በከተማይቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፥ የከተማይቱ ሕዝብ በሙሉ ወንድ ሴት ሳይባል ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣሪያ ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos