መሳፍንት 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፤ ኰረብታማ በሆነው በአማሌቃውያን አገር በኤፍሬም ምድር በጲርዓቶን ተቀበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፤ ኰረብታማ በሆነው በአማሌቃውያን አገር በኤፍሬም ምድር በጲርዓቶን ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ዓብዶን ሞተ፤ ኮረብታማም በሆነው በዐማሌቃውያን አገር በኤፍሬም ግዛት በምትገኘውም በፒርዓቶን ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤፍራታዊው የኤሎን ልጅ ለቦንም ሞተ፤ በተራራማውም በአማሌቃውያን ምድር በኤፍሬም ባለችው በኤፍራታ ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፥ በተራራማውም በአማሌቃውያን ምድር በኤፍሬም ባለችው በጲርዓቶን ተቀበረ። |
እርሱም በሰባ አህዮች ላይ የሚቀመጡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፤ በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈራጅ ሆነ።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።