Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 3:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እዚያም እንደ ደረሰ፥ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በእርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ አብረውት ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እዚያም እንደ ደረሰ፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ ዐብረውት ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እዚያም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንደ ደረሰ በኤፍሬም ተራራማው አገር የክተት እምቢልታ ነፋ፤ የእስራኤልም ሕዝብ በእርሱ መሪነት ተከትለውት ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በመጣም ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፥ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው አገር ወረዱ፥ እርሱም በፊታቸው ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 3:27
13 Referencias Cruzadas  

ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ።


ከዚያም የጌታ መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው።


ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።


ከዚህም በኋላ ሴቲቱ ብልኅ ምክሯን ይዛ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሼባዕን ራስ ቆርጠው ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ ስለዚህ ኢዮአብ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ከከተማዪቱ ርቀው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው ሄዱ፤ ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።


ሚካ የተባለ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር ሰው ነበር።


ጌዴዎንም በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፥ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ።


በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።


ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢኖሩአቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ።”


ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ብዙ ሕዝብስ ከሆንህ ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦህ እንደሆነ ወደ ዱር ወጥተህ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለአንተ ስፍራ መንጥር።”


የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ኤሁድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታ ይም አመለጠ።


ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ፥ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ሳምር በምትባል መንደር ይኖር ነበር።


የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ስፍራ በዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios