“እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’” አለው።
ኢያሱ 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በአቃሮን ሰሜናዊ ተረተር አድርጎ ወደ ሽክሮን ይታጠፍና በበኣላ ተራራ ላይ ዐልፎ እስከ የብኒኤል ይደርሳል፤ ከዚህ በኋላ ወሰኑ ባሕሩ ላይ ይቆማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ወደ ሽክሮን ደረሰ፥ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። |
“እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’” አለው።
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድነው? በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብለህ በማሰብህ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም! ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!’”
ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤
ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ዔቅሮን ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ዔቅሮን በገባ ጊዜም፥ የዔቅሮን ሕዝብ፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ያመጡብን እኛንና ሕዝባችንን ለማስፈጀት ነው” በማለት ጮኹ።
ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን እናድርገው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ ጋት ውሰዱት” አሏቸው። ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወሰዱት።
ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከዔቅሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ወርዶ ነበር።