ኢዩኤል 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዮ ለዚያ ቀን! የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ ከሁሉን ቻይ አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዮ! የጌታ ቀን ቀርቦአል! ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ደርሶአል። ስለዚያ ቀን ወዮ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እርሱም በጥፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል። |
ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ እርሱም ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።
ጌታም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ያሰማል፥ ሠራዊቱ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚፈጽም እርሱ ኃያል ነውና፥ የጌታ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?