La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፥ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ያለ ነቀፋ ብሆንም እንኳ፣ ስለ ራሴ ግድ የለኝም፤ የገዛ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምንም እንኳ ፍጹም ብሆን ስለ ራሴ አላስብም ሕይወቴንም እጸየፈዋልሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጹሕ ነኝ፤ ራሴ​ንም አላ​ው​ቅም፤ ነገር ግን ሕይ​ወቴ ጠፋች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፥ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 9:21
14 Referencias Cruzadas  

ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።


ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።


ለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፥ እግዚአብሔርን የጠራሁ እኔ፥ እርሱም የመለሰልኝ፥ ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል።


እነሆ፥ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ። ጽድቄም እንደሚገለጽ አውቃለሁ።


‘እኔ ንጹሕ ነኝ፥ በደል የለብኝም፤ ያለ እንከን ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፥


እግዚአብሔርም ያደቀኝ ዘንድ፥ እጁንም ለቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ ወድዶ ቢሆን ኖሮ!


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


ጻድቅ ብሆንም እንኳን ልመልስለት አልችልም፥ ፈራጄን እማጸናለሁ እንጂ።


በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፥ በጥበብ የሚመላለስ ግን ይድናል።


በራሴ ላይ ከኅሊናዬ ምንም የለም፤ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ግን ጌታ ነው።


ልባችን ቢወቅሰን እንኳ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።