እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል።
ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣ ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።
ትንፋሽ እስካገኝ እንኳ ፋታ አይሰጠኝም፤ ሕይወቴን በሥቃይ ሞልቶታል።
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገርን አጥግቦኛል።
የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
የመረረ ነገር ጽፈሕብኛልና፥ የልጅነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ።
“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
በመከራ ላሉት ብርሃን፥ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸው፥
የማትተወኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ።
ነገር ግን የልባቸውን እልከኝነትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን በኣሊምን ተከትለዋልና
ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ።
ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።
ለጊዜው ቅጣት ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰላማዊ የጽድቅን ፍሬ ያፈራላቸዋል።
እሷም፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ‘ማራ’ በሉኝ እንጂ ‘ናዖሚ’ አትበሉኝ።