አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ኢዮብ 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ ሥጋ ይልቅ ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣ መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሥቃይ የበዛበት ሰውነት ተሸክሜ ከመኖር ታንቄ መሞትን እመርጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትን ከመንፈሴ ትለያለህ። አጥንቶቼንም ከሞት ትጠብቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ መታነቅንና ሞትን መረጠች። |
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።