Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሕይወቴን እጸየፋለሁ፤ ዘላለም መኖር አልፈልግም፤ ዘመኔ እንደ እስትንፋስ ነውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ተስፋ ቈርጬአለሁ፤ መኖርም አልፈልግም፤ የሕይወቴም ዘመን አጭር ስለ ሆነ ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እን​ድ​ታ​ገሥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለ​ሁን? ሕይ​ወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘላለም ልኖር አልወድድም፥ የሕይወቴ ዘመን እስትንፋስ ነውና ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 7:16
22 Referencias Cruzadas  

“ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።


እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።”


የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?


ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፥ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።


እግዚአብሔርም ያደቀኝ ዘንድ፥ እጁንም ለቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ ወድዶ ቢሆን ኖሮ!


አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”


ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፥ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል።


ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፥ ዓመቶቻቸውም በሽብር።


ሕዝቦች ሆይ፥ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።


አንተ ሠርተኸኛልና ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም።


ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”


“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።


ከዚህ ሥጋ ይልቅ ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች።


ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፥ ሥጋም እንደ ሆኑ አሰበ።


እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህም ክፉ ወገን የቀሩትን ትሩፋን ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።


ከፀሐይም በታች የተሠራው ሥራ ሁሉ ከብዶብኛልና ሕይወትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios