እጠብቅ ዘንድ ጉልበቴ ምንድነው? እታገሥም ዘንድ ፍጻሜዬ ምንድነው?
“አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣ እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
በሕይወት ለመኖር የሚያበቃ ምን ብርታት አለኝ? ተስፋ ከሌለኝስ ለምን እኖራለሁ?
እታገሥ ዘንድ ጕልበቴ ምንድን ነው? ነፍሴም ትጽናና ዘንድ ዘመኔ ምንድን ነው?
እጠብቅ ዘንድ ጕልበቴ ምንድር ነው? እታገሥም ዘንድ ፍጻሜዬ ምንድር ነው?
የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
የረገፈውን ቅጠል ታስደነግጣለህን? ወይስ የደረቀውን ገለባ ታሳድዳለህን?
እኔ እንደሚበሰብስ የተበላሸ ነገር፥ ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ።”
መንፈሴ ደከመ፥ ቀኖቼ አለቁ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥ ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።
በውኑ የኀዘን እንጉርጉሮዬን ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሤ ተገቢ አይደለምን?
“ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
ጉልበቴ የድንጋይ ጉልበት ነውን? ሥጋዬስ ነሐስ ነውን?
አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለጌታ ይገዙ ዘንድ።
ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፥ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ፦
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።