ብረትን እንደ ገለባ፥ ናስንም እንደ ነቀዝ እንጨት ይቆጥራል።
ከአፉ ፍም ይወጣል፤ የእሳት ትንታግ ይረጫል።
ከአፉ የእሳት ነበልባል ይወጣል፤ የእሳት ፍንጣሪም ሲበተን ይታያል።
የናስ ፍላጻ ሊበሳው አይችልም፤ የወንጭፍ ድንጋዮችም በእርሱ ዘንድ እንደ ገለባ ናቸው።
ብረትን እንደ ገለባ፥ ናስንም እንደ ነቀዝ እንጨት ይቈጥራቸዋል።
ሰይፍና ጦር፥ ፍላጻና መውጊያም ቢያገኙት አያሸንፉትም።
ቀስት ሊያባርረው አይችልም፥ የወንጭፍም ድንጋዮች እንደ ገለባ ይሆኑለታል።
ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ ተናጉም እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና።