ኢዮብ 40:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፍርዴን ታቃልላለህን? ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ፍርደ ገምድል አድርገህ በመክሰስ ራስህን ንጹሕ ለማድረግ ትሞክራለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ፍርዴን መቃወምህን ተው፥ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን? |
ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፥ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም፤ የሚትረፈረፍ መቅሰፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ።
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
ይህንም እላለሁ፦ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ፥ የተስፋውን ቃል ለማስቀረት፥ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን ሊሽር አይችልም።