ኢዮብ 40:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥንቃቄ ሁሉን ተመልክተህ አሳፍራቸው፤ ክፉዎችንም ባሉበት ስፍራ አጥፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕቢተኛውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድርገው፤ ዝንጉዎችንም በአንድ ጊዜ አጥፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው። |
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።
በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ።