ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ።
ኢዮብ 38:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ብርሃን ተከልክለዋል፤ ለዐመፅ ያነሡአቸው ክንዶቻቸውም ተሰብረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣንን ብርሃናቸውን ከልክለሃልን? የትዕቢተኞችንስ ክንድ ሰብረሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል። |
ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ።
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ፥ የበረታችውንና የተሰበረችውን ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ እጥለዋለሁ።
ነገር ግን የአገሩ ተወላጅ ቢሆን ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በትዕቢት ማናቸውንም ነገሮች የሚያደርግ ሰው ጌታን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።