ኢዮብ 36:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የውኃውን ነጠብጣብ ወደ ላይ ይስባል፥ ዝናብም ከጉም ይንጠባጠባል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተንናል፤ መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ውሃን ከባሕር ወደ ላይ ይስባል፤ ከሰማይም ያዘንበዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዝናቡም ነጠብጣቦች በእርሱ ይቈጠራሉ። ዝናብም ከደመና ይንጠባጠባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የውኃውን ነጠብጣብ ወደ ላይ ይስባል፥ ዝናብም ከጉም ይንጠባጠባል፥ |
ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
የበልግ ዝናብ እንዲሰጣች ጌታን ለምኑ፤ መብረቁን ደመና የሚያደርግ ጌታ፥ ያደርጋል፥ እርሱም ለእያንዳንዱ የምድር ተክል የሚሆን ዝናብ ይሰጣል።