ኢዮብ 36:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ልዑል ነው፥ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን አስተውል፤ እግዚአብሔር ከሁሉ የበለጠ አስተማሪ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ ኀያሉ እግዚአብሔር በኀይሉ ያጸናል። እንደ እርሱስ ያለ ኀያል ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፥ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? |
ሁሉም ሰው ለበላይ ባለ ሥልጣናት ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።