ኢዮብ 34:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍትሕን እንምረጥ፥ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚበጀንን እንምረጥ፣ መልካሙንም ዐብረን እንወቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ የሆነውን ነገር መርምረን እንወቅ፤ መልካሙንም ነገር አብረን እንማር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ለራሳችን እንምረጥ፤ በመካከላችንም ምን እንደሚሻል እንወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፥ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ። |
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ያየም ሁሉ፥ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩ በት” ተባባሉ።